በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በግጭት ወቅት አርማው እንዲከበር የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር ጠየቀ


.
.

የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር በመከላከያ ሰራዊት እና ትግራይ ክልል ኃይሎች መካከል ጦርነት በሚደረግባቸው ቦታዎች ሰብአዊ ድጋፍ ለማድረግ ያሰማራቸው መኪኖች በጥይት መመታታቸውን አስታወቀ።

ማህበሩ ጦርነቱ በሚካሄድባቸው የአማራ ክልል እና ትግራይ ክልል አዋሳኝ ስፍራዎች አገልግሎቱን አሁንም መቀጠሉን ያወሱት የማህበሩ ቃል አቀባይ ዶ/ር ሰለሞን ዓሊ፣ ትግራይ ክልል ውስጥ ከሚገኘው ቅርንጫፍ ጋር ያላቸው ግንኙነት ቢቋረጥም ዓለም አቀፍ አሰራሮች በሚፈቅዱት መሰረት ተግባራቱን ያከናውናል ብለው ተስፋ እንደሚያደርጉ አስታወቀዋል።

ዶ/ር ሰለሞን ዓሊ የማህበሩን ተግባራት የሚያሳድጉ ድጋፎች ይበረክቱ ዘንድ ፣ ሁሉም አካላት በግጭት ወቅት የቀይ መስቀልን አርማ እንዲያከብሩ ጥሪ አቅርቧል።

ዶ/ር ሰለሞን ከዘጋቢያችን ሀብታሙ ስዩም ጋር ያደረጉት ቃለ-ምልልስ በመቀጠል ይሰማል

XS
SM
MD
LG