ዋሽንግተን ዲሲ —
አሜሪካዊያን ባሳለፍነው ጥቅምት 24.2013 ሀገሪቱን ለቀጣይ አራት ዓመታት የሚመሯትን ፕሬዚደንት ሲመርጡ ውለዋል። ወደ 100 ሚሊየን የሚጠጋው መራጭ በቅድመ -ምርጫ ሂደቱ አማካኝነት ድምጹን የሰጠ ቢሆንም ዛሬ ከማለዳው ጀምሮ ወደ ምርጫ ጣቢያዎች በማቅናት ድምጻቸውን የሰጡም ነበሩ። ዘጋቢያችን ሀብታሙ ስዩም በቨርጂኒያ ግዛት በሚገኝ አንድ ምርጫ ጣቢያ ተገኝቶ ሂደቱን ተከታተሏል።በተለያዩ ግዛቶች ውስጥ ከነበሩ ትውልደ -ኢትዮጵያዊያን መራጮችም ጋር ተጨዋውቷል።በመቀጠል ይሰማል።