ታሪኩ ደሳለኝ ለአሜርካ ድምፅ እንደገለፀው፤ ዛሬ ከሰዓት በኋላ የፖሊስ ደንብ ልብስየለበሱ እና ሲቪሎች ወደ መጽሔቱ ቢሮ ከደረሱ በኋላ ዋና አዘጋጁን አቶ ምስጋን ዝናቤንከያዙ በኋላ ወደ ተመስገን ደሳለኝ ስልክ እንዲደወል አድርገዋል።
ተመስገንን እንደሚፈልጉት እና ወደ ቢሮ እንዲመጣ ከነገሩት በኋላ፤ ቢሮ ሲደርስሁለቱንም ይዘዋቸው ወደ አዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን እንደወሰዷቸው ተናግሯል።
ማምሻውን አዲስ አበባ ፖሊስ ሄደው መታሰራቸውን ከሩቁ እንዳረጋገጠም ተናግሯል።በጉዳዩ ላይ ከአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ምላሽ ለማግኘት ያደረግነው ጥረት አልተሳካም።በነገው ዕለት ዘርዝር ያለ መረጃ ይዘን እንመለሳለን።