በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የተተቸው ፕሬዚዳንታዊ ክርክር


የመጀመሪያው ፕሬዚዳንታዊ ክርክር
የመጀመሪያው ፕሬዚዳንታዊ ክርክር

ፕሬዚዳናት ዶናልድ ትራምፕ እና የቀድሞ ም/ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን በተጧጧፈውና ዘለፋ ጭምር በተለዋወጡበት በትላንቱ ማክሰኞ ምሽት፣ የመጀመሪያው ፕሬዚዳንታዊ ክርክራቸው የፖሊሲ ሀሳቦቻቸውን አቅርበዋል፡፡ ክርክሩ የተካሄደው ለምርጫው አምስት ሳምንታት ሲቀሩት ነው፡፡

የተተቸው ፕሬዚዳንታዊ ክርክር
please wait

No media source currently available

0:00 0:06:14 0:00


ደህና በሚባል የሰላምታ ልውውጥ የተጀመረው ክርክር፣ በጉዳዮች ላይ ወደ ተነሳው የጦፈ ክርክር የገባው ወዲያው ነበር፡፡ በመላው ዓለም አንድ ሚሊዮን፣ በዩናይትድ ስቴት ደግሞ ከ200ሺ በላይ ሰዎችን ህይወት የቀጠፈው የኮቪድ 19 ጉዳይ አንዱ መነጋገሪያ ሆኗል፡፡ የዴሞክራቲክ ፓርቲ ፕሬዘደንታዊ እጩ ፣ ጆ ባይደን እንዲህ አሉ፤

“ፕሬዚዳንቱ ምንም እቅድ የላቸውም፡፡ ምንም ያቀዱት ነገር ነው፡፡ ካለፈው የካቲት ጀምሮ ይህ ቀውስ ምን ያህል ከባድ እንደነበር ያውቁ ነበር፡፡”

ፕሬዚዳንት ትራምፕ ደግሞ በበኩላቸው ለችግሩ የተሳካ ምላሽ እንዲገኝ ያደረጉ መሆናቸውን ሲገልጹ ፤

“የሆስፒታል አልባሳትን አቅርበናል የፊት ጭንብሎችን አቅርበናል፡፡ የመተንፈሻ መሳሪያዎችን (ቬንትሌተሮችን) አቅርበናል፡፡ እናንተ እነዚህ የመተንፈሻ መሳሪያዎች አይኖራችሁም ነበር፡፡ አሁን ደግሞ ለከትባቱ ሳምንታት ብቻ ናቸው የቀሩን፡፡” ብለዋል፡፡

ባይደን፣ ፕሬዚዳንት ትራምፕ፣ ለ20 ሚሊዮን አሜሪካውያን፣ የጤና መድህን ይሰጣል ያሉትን ፣ ኦባማ ኬር እየተባለ የሚጠራውንና፣ ተመጣጣኝ የጤና እንክብካቤ ህግ እንዲቋረጥ ይፈልጋሉ በማለት ከሰዋቸዋል፡፡

ፕሬዚዳንት ትራምፕ ደግሞ፣ ህጉ፣ ህገመንግስታዊ አይደለም፡፡ ለተጠቃሚዎችም አማራጮችን የሚያሳጣ ነው ብለውታል፡፡ ባይደን በበኩላቸው፣ እሳቸው በሚያስፋፉት ኦባማ ኬር ስር፣ መራጮች የግላቸውን የጤና መድህን ይዘው መቀጠል “ይችላሉ፡፡ ያደርጉታል፡፡ በእኔ እቅድ ውስጥ ያሉ ናቸው፡፡” ብለዋል፡፡

የመጀመሪያው ፕሬዚዳንታዊ ክርክር
የመጀመሪያው ፕሬዚዳንታዊ ክርክር

ክርክሩ አንዳቸው አንዳቸውን ሳያስጨርሱ ጣልቃ መግባት የበዛበት ነበር፡፡ ብዙ ጊዜ ጣልቅ የሚገቡት ፕሬዚዳንት ትራምፕ "ኦባማ ኬር ጥሩ አይደለም፡፡ የተሻለ አድርገነዋል፡፡” በማለት አጣጥለውታል፡፡

ትራምፕ፣ ባይደን የህክምና አገልግሎትን በመውረስ የህዝብ ማድረግ ይፈልጋሉ በማለት ከሰዋቸዋል፡፡ ብርቱ ክርክር የቀሰቀሰው ሌላኛው ነጥብ፣ በቅርቡ የሞቱትን የጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኛ፣ ሩት ባዴር ጊንስበርግን ለመተካት፣ ፕሬዚዳንት ትራምፕ ያቀረቧቸው እጩ ነበሩ፡፡ ትራምፕ በእጩነት ያቀረቡት ወግ አጥባቂዋን ዳኛ ኤሚ ኮኒ ባረትን ሲሆን፣ ዕጩነታቸውን እንዲጽደቅ የተፈለገው፣ በብዙ ክፍለ ግዛቶች መራጮች ድምጽ መስጠት በጀመሩበት ወቅት ነው፡፡

ባይደን የጊንስበርግ ቦታ መሙላት የሚችለው በሚቀጥለው ህዳር የሚያሸነፈው ሰው ነው፣ “የአሜሪካ ህዝብ የጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ዳኛ ማን መሆን እንዳለበት የመወሰን መብት አለው፡፡” ብለዋል፡፡

ፕሬዚዳንት ትራምፕ ግን ጊዜው ምንም ይሁን ምን ክፍት የሆነውን ቦታ መሙላት የሳቸው ኃላፊነት መሆኑን በመግለጽ ምርጫውን አሸንፈናል፡፡ ስለዚህ እሳቸውን ለመምረጥ መብት አለን፡፡ በማለት ተናግረዋል፡፡

የትራምፕ፣ የምረጡኝ ዘመቻ ኃላፊ ቲም ማርታፍ፣ በክርክሩ ውጤት ደስተኛ መሆናቸውን ገልጸው፣ "ተመልካቾች ያዩት ነገር ቢኖር ፕሬዚዳንት ትራምፕ እያንዳንዱን የክርክር እንቅስቃሴ የተቆጣጠሩ መሆኑን ነው፡፡ እኔ እንደሚመስለኝ በአብዛኛው ባይደን ደካማ መሆናቸውንና ዙሪያውን እየተመለከቱ የሚያወያየውን ሰው እርዳታ ሲማጸኑ የተመለከቱ ይመስለኛል፡፡" ብለዋል፡፡

"ባይደን ሲናገሩ ብዙ ጊዜ ለ10 ፣20 እና 30 ሰከንዶች ነጥቦቻቸውን ሳያዛንፉ የሚናገሩበትን እድል ያገኛሉ፡፡ ከዚያ በኋላ ግን በየመሃሉ ጣልቃ በሚገቡት ፕሬዚዳንት ትራምፕ፣ ንግግራቸውን አሁንም አሁንም ደጋግመው ለማቋረጥ ይገደዳሉ፡፡ ስለዚህ በዚህ ፕሬዚዳንታዊ ክርክር ማን አሸነፈ ለማለት አይቻልም፡፡ ምክንያቱም ፕሬዚዳንቱ በእርግጠኝነት ምንም ዓይነት ፕሬዚዳንታዊ ክርክር እንዳይኖር አድርገዋል፡፡"

ተናንታኞች ግን በክርክሩ ማንም አሸናፊ አለመኖሩን ይናገራሉ፡፡ ከጆርጅ ሜሰን ዩኒቨርስቲ ጀሚ ሜየር ፤ "ባይደን ሲናገሩ ብዙ ጊዜ ለ10 ፣20 እና 30 ሰከንዶች ነጥቦቻቸውን ሳያዛንፉ የሚናገሩበትን እድል ያገኛሉ፡፡ ከዚያ በኋላ ግን በየመሃሉ ጣልቃ በሚገቡት ፕሬዚዳንት ትራምፕ፣ ንግግራቸውን አሁንም አሁንም ደጋግመው ለማቋረጥ ይገደዳሉ፡፡ ስለዚህ በዚህ ፕሬዚዳንታዊ ክርክር ማን አሸነፈ ለማለት አይቻልም፡፡ ምክንያቱም ፕሬዚዳንቱ በእርግጠኝነት ምንም ዓይነት ፕሬዚዳንታዊ ክርክር እንዳይኖር አድርገዋል፡" ሲሉ አስተያየት ሰጥተዋል፡፡

ትናንት ምሽት በሪፐብሊካን ዕጩ ፕሬዚዳንት ትራምፕ እና በዴሞክራቲኩ ተፎካካሪያቸው በቀድሞ ም/ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን መካከል በተካሄደው ክርክር ዙሪያ ያለው አስተያየት በፓርቲዎች ወገንተኝነት የተከፈለ ነው፡፡ ይሁን እንጂ፣ የክርክር መድረኩ፣ ሁሉም ያለ ተጠያቂነት፣ እንዳሻቸው የሚናገሩበት እየሆነ መምጣቱም፣ ጠንካራ ትችት አስነስቷል፡፡ የሪፖርብሊካን ፓርቲ ብሄራዊ ኮሚቴ ሊቀመንበር፣ ሮና መክ ዳንኤል እንዲህም በቲውት ገጻቸው የሚከተለውን አስፍረዋል ለዘጠና ደቂቃ ፕሬዚዳንት ትራምፕ በራስ መተማመን ነበራቸው፡፡ ለምን በድጋሚ መመረጥ እንደሚገባቸውም ምክንያታቸውን በሚገባ አቅርበዋል፡፡ ታክስ እንዲጨመር የሚያደርገውን፣ ሥራ የሚያጠፋውንና የማህበረሰቡን የበለጠ ለአደጋ የሚያጋልጠውን የጆ ባይደን ስር ነቀል ፖሊሲዎቻቸውን በሚገባ የተቹ ይመስለኛል፡፡

ተሰሚነት ያላቸው ዴሞክራቶችም የቀድሞ ም/ፕሬዚዳንት ጆ ባይደንን የክርክሩ አሸናፊ በማድረግ፣ ፕሬዚዳንት ትራምፕ ለሁለተኛ ጊዜ እንዳይመረጡ አሳማኝ ምክን ያት ማቅረባቸውን ተናግረዋል፡፡ ቀደም ሲል በማጣሪያው ምርጫ የዴሞክራቲክ እጩ ተወዳዳሪ ሆነው ከባይደን ጋር ተፎካካሪ የነበሩት፣ የኒው ጀርሲው ሴነተር ኮሪ ቡከር፣ በቲውት ገጻቸው ላይ ባሰፈሩት ጽሁፍ የትራምፕን ንግግር ነቅፈዋል፡፡ ፕሬዚዳንት ትራምፕ የነጭ የበላይነትን የሚያራምዱ ወገኖችን በይፋ ማውገዙን ያልተቀበሉ ሲሆኑ፣ እንዲያውም የሳቸው ደጋፊዎች እንዲሆኑ መጋበዛቸውን በክርክራቸው አመላክተዋል፣ በማለት የኮነኑት ኮሪ ቡከር “ዶናልድ ትራምፕ በቅጥፈታቸው፣ በጎጠኝነታቸው፣ በአደገኛውና ግድየለሽ አመራራቸው ይህን አገር አዋርደዋል፡፡” በማለት ኮንነዋቸዋል፡፡

ክርክሩን የተከታተሉ በርካታ ሰዎች፣ በሁለቱ ዕጩዎች መካከል የተካሄደው ክርክር፣ መጯጯህ የበዛበት መሆኑን ተናግረዋል፡፡ ከእነዚህ አንዷ የሆኑት የዋሽንግተን ፖስት ጋዜጣ የዓለም አቀፍ አስተያየቶች ኤዲተር፣ ካረን አቲሃ ክርክሩን “ አገራዊ ውርደት” ብለውታል፡፡

የመጀመሪያው ፕሬዚዳንታዊ ክርክር መሪና የፎክስ ኒውስ የዜና አቅራቢ ክሪስ ዋለስ
የመጀመሪያው ፕሬዚዳንታዊ ክርክር መሪና የፎክስ ኒውስ የዜና አቅራቢ ክሪስ ዋለስ

(ግጭት የተሞላበት ነው የተባለውን ክርክር የቪኦኤው ዘጋቢዎች Mike O’Sullivan ,Richard Green, Carolyn Presutti አዘጋጅተውታል ደረጀ ደስታ ደግሞ በአማርኛ አጠናቅሮታል​)

XS
SM
MD
LG