ዋሽንግተን ዲሲ —
ባሳለፍነው ሳምንት መጨረሻ ጀምሮ በቤተሰብ ዕቅድ እና በስነ-ተዋልዶ ጤና ላይ ለዓመታት በሰራቸው ስራዎች የሚታወቀው ዲኬቲ ኢትዮጵያ ለየት ያለ የበይነ -መረብ ላይ ትርኢት እያሳየ ይገኛል።
ትርኢቱ ደግሞ በዕውቅ የፋሽን ንድፍ ባለሙያዎች የተዘጋጁ የአፍ እና አፍንጫ መሸፈኛዎች የሚታዩበት ነው።
ሀብታሙ ስዩም ያናገራቸው የድርጅቱ የገበያ ዘርፍ ሃላፊ ወ/ሮ እመቤት አቡ የትርኢቱ ዓላማ ወጣቶች ጤናቸውን እየጠበቁ ሊደምቁባቸው ከሚችሉባቸው መላዎች ጋር ማስተዋወቅ እንደሆነ ጠቁመዋል።
ሙሉ ቃለ-ምልልሱን ያዳምጡ፦