በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

“የቀረበው ስሞታ በዓለም አቀፍ አሰራር ተቀባይነት ያለው አይደለም” -ም/ጠ/ዐ/ህግ ፍቃዱ ጸጋ


የኢፌዲሪ ምክትል ጠቅላይ ዐቃቢ ህግ አቶ ፍቃዱ ጸጋ
የኢፌዲሪ ምክትል ጠቅላይ ዐቃቢ ህግ አቶ ፍቃዱ ጸጋ

የኢፌዲሪ ጠቅላይ ዐቃቢ ህግ ሂዩማን ራይትስ ዋች የተሰኘው የመብት ተሟጋች ድርጅት ከሰሞኑ ያወጣውን በቁጥጥር ስር የሚገኙ ፖለቲከኞች እና ጋዜጠኞችን የሚመለከት መግለጫ የሀገሪቱን የፍትህ ስርዓት ጠንቅቆ ባለማወቅ እና በችኮላ የተሰጠ ነው ሲል አስተባብሏል።።

ሂዩማን ራይትስ ዋች በሪፖርቱ የምርመራ ሂደቱ የተጓተተ እና ፍትሃዊውን አሰራር የጣሰ ነው ይላል። በርካታ ታሳሪዎች ከቤተሰቦቻቸው እና ጠበቆቻው ጋር እንዳይገናኙ ተደርጓል በሚልም ወቅሷል።ፍርድ ቤት በዋስትና እንዲለቀቁ የፈቀደላቸውን ግለሰቦች ፖሊስ ግን በራሱ ስልጣን በእስር ያቆያል በሚልም ተችቷል። በእስር የሚገኙ ጋዜጠኞችን እና ፖለቲከኞችን ለጤና ስጋት የሚዳርግ አሰራር ሊቀረፍ ይገባል የሚል ማሳሰቢያም ሰጥቷል።

ከአሜሪካ ድምጽ ጋር ቆይታ ያደረጉት ምክትል ጠቅላይ ዐቃቢ ህግ ፍቃዱ ጸጋ፣ በእስር ላይ የሚገኙ ፖለቲከኞች እና ጋዜጠኞች እየገጠማቸው ነው ተብለው የተዘረዘሩ የመብት ረገጣዎችን በተመለከተ ምላሽ ሰጥተዋል።

ከአቶ ፍቃዱ ጸጋ ጋር የተደረገውን ሙሉ ቆይታ ያዳምጡ።

“የቀረበው ስሞታ በዓለም አቀፍ አሰራር ተቀባይነት ያለው አይደለም” -ም/ጠ/ዐ/ህ ፍቃዱ ጸጋ
please wait

No media source currently available

0:00 0:15:40 0:00


XS
SM
MD
LG