የመጫና ቱለማ መረዳጃና ልማት ሕዝባዊ ማኅበር ፕሬዚዳንት መደብደባቸውን ገለፁ
የመጫና ቱለማ መረዳጃና ልማት ሕዝባዊ ማኅበር ፕሬዚዳንት አቶ ድርቤ ደምሴ ባለፈው ሣምንት ውስጥ መኖሪያ ቤቴ ውስጥ“በመንግሥት ፀጥታ አስከባሪዎች ተደብድቤአለሁ” ሲሉ ስሞታ አሰምተዋል።የከተማው የፀጥታና የአስተዳደር ፅህፈት ቤት ኃላፊ ስብሰባ ላይ መሆናቸውን ገልፀው ምላሽ ሊሰጡ እንደማይችሉ የተናገሩ ሲሆን ፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ስለጉዳዩ መረጃ እንዳልደረሰው ገልጿል።የኦሮምያ ክልል የመንግሥት ኮምዩኒኬሽንስ ቢሮ በበኩሉ ስለጉዳዩ አጣርቶ ማብራሪያ እንደሚሰጥ አስታውቋል።