በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ስለ ተግባቦት እክል ፦ቆይታ ከንግግር እና ቋንቋ ሀኪም ማህሌት አዘነ ጋር


.
.

በመላ ዓለም ላይ ከድምጽ ፣ንግግር ፣ ቋንቋ እክል ጋር የሚኖሩ ህጻናት እና አዋቂዎች ቁጥር ጥቂት አይደለም። ለአብነት የዮናይትድ ስቴትስ ብሄራዊ መስማት የተሳናቸው እና ሌሎች ተግባቦት ችግሮች ተቋም ከአራት ዓመት በፊት የጠቀሰውን ጥናት ብናይ ከ12 ልጆች መካከል አንዱ እክሉ እንደሚገጥመው ያስረዳል።

ኢትዮጵያ ውስጥ የችግሩን አድማስ የሚያሳይ ጥናት ወጥ ጥናት ባይገኝም ፣ ማህሌት አዘነን የመሰሉ በሀገሪቱ ያሉ ጥቂት የንግግር እና ቋንቋ ግድፈት ሀኪሞች ግን በርካታ ህጻናት እና አረጋዊያን ከችግሩ ጋር እየኖሩ እንደሆኑ ይጠቁማሉ።

ማህሌት አዘነ በተለያዩ ስነልቦናዊ እና አካላዊ ምክንያቶች ለመናገር የሚቸግራቸውን ኢትዮጵያዊያን የሚረዳ አገልግሎት ትሰጣለች። ስለ ችግሩ ማህበረሰባዊ ንቃትን ለመፍጠር በማህበራዊ መገናኛዎች ላይ ዕውቀቷን ታጋራለች።

በተያያዥ ጉዳዮች ላይ ከቪኦኤ ጋቢና መሰናዶ ጋር ያደረገችውን ቆይታ ያዳምጡ።

ቆይታ ከንግግር እና ቋንቋ እክል ሀኪም ማህሌት አዘነ ጋር
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:25 0:00


XS
SM
MD
LG