ዋሽንግተን ዲሲ —
የዘመን ተጋሪዎቹ ከሚያከታትሏቸው የሙዚቃ ርዕሰ ጉዳዮች ለየት ያሉ ሀሳቦችን ያቀነቅናል። የሙዚቃ ዘይቤውንም ለመጀመሪያ ጊዜ የሰሙ በርግጥ ልዩ ነገር ይዞ ስለመምጣቱ ይሰማቸዋል።
ወጣቱ የሙዚቃ ሰው ዳዊት ቸርነት በአማርኛ እና እንግሊዝኛ ቋንቋ ስራዎቹ ፍቅርን ይሰብካል ፣ ፍትህን ይጠይቃል፣ ሰብአዊነትን ይመረምራል።ጊታሩን እየኮረኮረ የሚያወጣቸው ጥሞና ደጋፊ ዜማዎች፣ አሊያም ኮርኮሪ ግጥሞች ግባቸው ፈጣን የገበያ ላይ ስኬት አይመስልም፣ ቀስ በቀስ የሚታይ ማህበረሰባዊ ለውጥ፣ የሰብአዊነት መጎልበት እንጂ።ዳዊት የዛሬው የጋቢና መዝናኛ እንግዳ ነው።መልካም ቆይታ።