ዋሽንግተን ዲሲ —
በዛሬው የጋቢና መዝናኛ |
ትውልድ እና ዕድገቱ መሃል አዲስ አበባ ነው።በህጻንነት አዕምሮው ወለል ላይ የታተሙ ምስሎችን የኃላ ኃላ በሸራ ላይ ቡርሽ እና ቀለምን አገናኝቶ ነፍስ በዘራባቸው ጊዜያት ግን ከመላው ኢትዮጵያም ሆነ ዓለም ብዙ አድናቂዎች እና ወዳጆችን አትርፏል።
ስዩም አያሌው ሰዓሊ፣ መመምህር፣ የዕይታ ጥበብ ባለሙያዎች መብት ተሟጋች የፍሬ ሀሳቦች ባለቤትም ነው።ዕውናዊ ስዕሎቹ በትዝታ፣ በሀዘን ፣ በጥሞናና መደመም ውስጥ የሚያመላልሱ ናቸው።
የኪነጥበብ መንገዱን በጥቂቱ ይተርክልን ዘንድ፣ በተያያዥ ሀሳቦች ላይ ዕይታውን ያካፍለን ዘንድ ፈቅዷል።ኪናዊ ወሬዎች እና የተመረጡ ሙዚቃዎችም ይሰማሉ። አብራችሁን ቆዩ።