ዋሽንግተን ዲሲ —
አባስ ሁሴን በዋሺንግተን ዲሲ እና አካባቢዎ ከ20 ዓመት በላይ የኖረ ትውልደ ኢትዮጵያዊ ነው። አባስ ከሚታወቅበት የንግድ እንቅስቃሴ በተጨማሪ ትውልደ-ኢትዮጵያዊያንን በሚያግዙ የበጎ አድራጎት ስራዎችም ንቁ ተሳታፊነቱ ይታወቃል።
የኮቪድ 19 መስፋፋትን ተከትሎ አባስ እንደለመደው ከኢትዮጵያ ዲያስፖራ ሙስሊም ማህበረሰብ ጋር ተሰባስቦ የኢድ -አል -አድሃን በዓል ማክበር ባይችልም፣ ያለፉ በዓሎችን ትዝታዎች እየዘከረ ከቤተሰቦቹ ጋር በዓሉን ለማሳለፍ እንደጣረ ለአሜሪካ ድምጽ ራዲዮ ተናግሯል።
ሀብታሙ ስዩም እና አባስ ሁሴን በተዛማች ጉዳዮች ላይ ያደረጉትን ቆይታ ያዳምጡ።