በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ስለ ጸረ-ጥላቻ ንግግር መረብ ፤ ምጥን ቆይታ ከዮሐንስ ሞላ ጋር


.
.

"የጸረ-ጥላቻ ንግግር መረብ" የተሰኘ የበጎ ፈቃደኞች ስብስብ ኢትዮጵያዊያን በሚያዘወትሯቸው የማህበራዊ መገናኛዎች ላይ መስመር የለቀቁ ናቸው ያላቸውን መረጃዎች በመንቀስ ርምጃ እንዲወሰድባቸው እያደረገ ስለመሆኑ ተሰምቷል።

በዚህ መረብ ውስጥ ተሳታፊ ከሆኑት መካከል አንዱ ገጣሚው እና የማህበራዊ ለውጥ አራማጁ ዮሐንስ ሞላ ነው። ዮሐንስ በግሉ አንድ ህዝብን ከአንደኛው ያጋጫሉ፣ ግጭት እና አልቂትን ይሰብካሉ ያላቸውን መረጃዎች ፌስቡክን ለመሰሉ ተቋማት በማመልከት ከማህበራዊ ገጾች ላይ እንዲወገዱ አድርጓል።

አሁን ላይ ደግሞ ከሌሎች ጋር በመተባበር መሰል ዘመቻዎችን ቀጥለዋል። ሀብታሙ ስዩም በሰሞነኛው ዘመቻ እና ተያይዘው በሚነሱ ሀሳቦች ዙሪያ ለመነጋገር ወደ ዮሐንስ ሞላ ደውሏል።

ስለ ጸረ-ጥላቻ ንግግር መረብ ፣ ምጥን ቆይታ ከዮሐንስ ሞላ ጋር
please wait

No media source currently available

0:00 0:10:06 0:00


XS
SM
MD
LG