በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በዋሺንግተን ዲሲ ስለተደረጉ ሰልፎች


.
.

ዛሬ በዋሺንግተን ዲሲ ከተማ ኢትዮጵያዊያን እና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን ሁለት ሰላማዊ ሰልፎች አድርገዋል። የመጀመሪያው ኢትዮጵያ ውስጥ ከሰሞኑ የደረሰውን የሕይወት እና ንብረት ውድመት የሚያወግዝ እና የጠ/ሚ አቢይ አህመድ አስተዳደር ሕግን ለማስከበር እየወሰደ ነው የተባለውን ርምጃ ለመደገፍ የተጠራ ነው።

ሁለተኛው ደግሞ ከተለያዩ የዩናይትድ ስቴትስ ግዛቶች እንደመጡ የሚናገሩ ወጣቶች፣ የታሠሩ የፖለቲካ እስረኞች ይፈቱ፣ ከእነ አቶ ጃዋር መሐመድ ጋር በመገኘታቸው ብቻ ያለ ጥፋታቸው የታሰሩ ሦስት የአሜሪካ ዜጎች በአስቸኳይ እንዲፈቱ እና ኢትዮጵያ ውስጥ የተፈፀመው የሰብዓዊ መብት ጥሰት በገለልተኛ አካል እንዲጣራ የሚጠይቅነው።

የሁለቱንም ሰልፎች አስተባባሪዎች ዘገቢዎቻችን አነጋግረዋቸዋል። ሀብታሙ ስዩም የመጀመሪያውን ሰልፍ ፣ጽዮን ግርማ ደግሞ ሌላኛውን ሰልፍ ይዘቶች አከታትለው ያሰሙናል።

በዋሺንግተን ዲሲ ስለተደረጉ ሰልፎች
please wait

No media source currently available

0:00 0:12:26 0:00


XS
SM
MD
LG