ዋሽንግተን ዲሲ —
መንግስት ቀደም ባሉት ጊዜያት ዲሞክራሲን ለማስለመድ ያሳይ የነበረው ታጋሽነት አሁን ሀገሪቱ ላለችበት ውጥረት ተጨማሪ አሉታዊ አስተዋጽኦ ማበርከቱን ጠቅላይ ዐቃቢ ህግ አዳነች አቤቤ ተናገሩ።ጠቅላይ ዐቃቢ ህግ አዳነች በአሁኑ ሰዓት "ከህግ ማስከበር ውጭ ምንም አማራጭ የለንም!" ብለዋል።
በድምጻዊ ሀጫሉ ሁንዴሳ ግድያ ተሳትፎ እና ከግድያው በኃላ ከተፈጠሩ ክስተቶች ጋር በተያያዘ በቁጥጥር ስር የዋሉ ግለሰቦች የተፋጠነ ፍትህ እንዲያገኙ ተቋማቸው እየሰራ መሆኑንም ተናግረዋል።አቶ ጃዋር መሀመድ፣ አቶ በቀለ ገርባን እና አቶ እስክንድር ነጋን ለመክሰስ የሚያበቃ በቂ ማስረጃ መገኘቱንም አውስተዋል።
ወ/ሮ አዳነች አቤቤ በተለይ ከቪኦኤ ጋር ያደረጉት ቃለምልልስ ሙሉ ቅጂ በመቀጠል ይሰማል።