በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

አስራት በጠቅላይ ዐቃቢ ህግ የቀረበበትን ክስ አስተባበለ


.
.

ከሰሞኑ በነበረ የኢትዮጵያ የጸጥታ ባለስልጣናት ስብሰባ ላይ ፣ የድምጻዊ ሀጫሉ ሁንዴሳን ግድያ ተከትሎ በተፈጠው ግጭት እና ውጥረት ማግስት ተቋማቸው እየወሰደ ያለውን እርምጃ ከአስረዱት መካከል አንዷ የኢፌዲሪ ጠቅላይ አቃቢ ወ/ሮ አዳነች አበቤ ናቸው።

እሳቸው የመገናኛ ብዙሀንን በተመለከተ ተወሰደ ባሉት እርምጃ ውስጥ ስማቸውን ከጠቀሷቸው መካከል የአማራ ሳተላይት ራዲዮ እና ቴሌቭዥን በምህጻሩ አስራት አንዱ ነው።

ወ/ሮ አዳነች አስራት ቴሌቭዥን፣ የአሮሚያ ሚዲያ ኔትወርክ እና ድምጸ-ወያኔ የሚዲያ ተቋማት ህዝቦች እርስ በርሳቸው እንዲጠራጠሩ፣እንዲቃቃሩ እና እንዲጋጩ በሚያደርጉ የመረሣ ስርጭቶች ውስጥ መሳተፋቸውን በመጥቅስ ምርመራ እንደተጀመረባቸው እና መስሪያ ቤቶቻቸውም እንዲፈተሹ እንደተደረገ ተናግረዋል።

የአስራት ቦርድ ም/ሊቀመንበር የሆኑት አቶ ተፈሪ አድማሱ ግን ተቋማቸው ከተመሰረተበት ቀን ጀምሮ የሀገሪቱን የብሮድካስት ህግ አክብሮ ፣ ሙያዊ ስነ-ምግባርን ጠብቆ ሲሰራ እንደቆየ በማውሳት ከተጠቀሱት መገናኛ ብዙሃን ጋር አብሮ መከሰሱ ትክክል እንዳልሆነ ተሟግተዋል።

አስራት በገጠሙት እክሎች ምክንያት ከሁለት ሳምንታት በፊት ጀምሮ ስርጭት ማቆሙን በማስታወስም ፣ ከሰሞነኛው ውጥረት እና ግጭት ጋር ተገናኝቶ መወቀሱንም ተቃውመዋል።

ሙሉ ዘገባውን ያዳምጡ።

አስራት በጠቅላይ ዐቃቢ ህግ የቀረበበትን ክስ አስተባበለ
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:57 0:00


XS
SM
MD
LG