ዋሽንግተን ዲሲ —
በዛሬው የጋቢና መዝናኛ፣ "ኢሻራ" እና "መደድ" በተሰኙ የግጥም እና አጫጭር ወግ መድብሎቹ የምናውቀው፣ ለበርካታ ሙዚቀኞች በሰጣቸው ብስል የዘፈን ግጥሞቹ የሚደነቀው ኑረዲን ኢሳ አብሮን ያመሻል። የኢትዮቲዩብ አውታር መስራች የሆነው ዓለማየሁ ገመዳ በቅርቡ ህይወቱ ያለፈውን ድምጻዊዊ አጫሉ ሁንዴሳን የሚያስታውሱ ሀሳቦችን ያካፍለናል። ትኩስ ኪናዊ ዜናዎች ከጥዑም የሙዚቃ ምርጫ ጋርም ይቀርባል።መልካም ቆይታ።