በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

"ሀጫሉ የማንንም ሰው ዕድገት የሚፈልግ ሙዚቀኛ ነበር" ገመቹ ደገፋ


.
.

በተለያዩ ጊዜያት ከድምጻዊ ሀጫሉ ሁንዴሳ ጋር ከሰሩ የኪነጥበቡ ዓለም ሰዎች አንዱ ገመቹ ደገፋ ነው።በርካታ የኢትዮጵያ ሙዚቀኞችን ወደ ሰሜን አሜሪካ በማስመጣት በካናዳ እና በዮናይትድ ስቴትስ እየተዘዋወሩ ዝግጅታቸውን እንዲያያቀርቡ ሲያደርግ የነበረው ገመቹ ሀጫሉን ከ10 ዓመታት በላይ ያውቀዋል።

በኦሮምኛ ቋንቋ በሰራቸው ሙዚቃዎች የብዙሃንን ቀልብ የሳበው፣ በፖለቲካ ቀመስ አስተያየቶቹ በተደጋጋሚ የሙግት ማዕከል የነበረውን ወጣቱን የኪነ ጥበብ ሰው ገመቹ «የማንንም ዕድገት የሚፈልግ ሙዚቀኛ ነበር» ሲል ይገልጸዋል።

ቅርበት እና ዕውቂያቸው ምክንያት ሆኖ የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን መቆጣጠር የተሳነው የሚመስለው ገመቹ ወደ ማህበራዊ መገናኛዎች ወጥቶ በዕምባ የታጀቡ አፍታዎችን ሲያሳልፍ ታይቷል።ከዚህ ተሻግሮ ግን ገመቹ የድምጻዊውን ሞት የተከተለው የግጭት መንፈስ ይወገድ ዘንድ አድናቂዎቹን እና ወዳጆቹን ጠይቋል። "ሁላችንም ተባብረን፣ ተያይዘን የምንኖር ህዝቦች ስለሆን ፣ማንም ማንም ላይ ጣት ሳይቀስር ፣እግዚአብሄር ምህረት እንዲያመጣልን ጸሎት ያስፈልጋል. . .ማንም ማንንም አይግደል" ሲል ተማጽኗል።

መንግስትም የኪነጥበብ ሰዎችን ደህንነት እንዲያስጠብቅ አሳስቧል።

የአሜሪካ ድምጹ ሀብታሙ ስዩም ከገመቹ ደጋፉ ጋር የነበረው ቆይታ በሚከተለው መልኩ ተቀናብሯል።

ሀጫሉ ሁንዴሳ በስራ አጋር ዐይን
please wait

No media source currently available

0:00 0:06:28 0:00


XS
SM
MD
LG