No media source currently available
የሶማሊያ ፌደራል መንግሥትና ከዓመታት በፊት ራሷን ነፃ ሪፐብሊክ ስትል ያወጀቸው ሶማሊላንድ መሪዎች ታሪካዊ መሆኑ በተነገረለት ስብሰባ ትናንት ጎረቤት ጅቡቲ ላይ ተገናኝተው ተነግጋረዋል። የሁለቱ መሪዎች ድርድር በጅቡቲው ፕሬዝዳንት ኢስማይል ኦማር ጊሌ አስተናጋጅነት ነው የተካሄደው።