በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ቴክኖሎጂ እና የመጻኢ ዘመን ስራ ገበያ ፦ ቆይታ ከአዱኛ በቀለ ጋር


ከ14 ዓመታት በተሻገረ የሙያ ዘመኑ የዛሬ እንግዳችን አዱኛ በቀለ የራሱን አሻራ የተወባቸውን ስራዎቹ በርካቶች ናቸው። የአሜሪካ ደህንነት መስሪያ ቤት ድረገጽ ማሻሻያ ግንባታዎች ከፍተኛ አበልጻጊ (senior developer)ሆኖ ሰርቷል። የሜሪላንድ የኒቪርሰቲ ፣ማርዮት ፋውንዴሽን ፣ ዋተር ሴንስ እና ሌሎች ዘርፈ ብዙ ተቋማትን ድረ-ገጽ በዋናነት ገንብቷል። በአሁኑ ሰዓት ኢቫንጋዲ ቴክ የተሰኘ ድርጅት መስርቶ በዲጂታል ግብይት፣ቴክኖሎጂካዊ ትስስር እና መሰል ጉዳዮች ላይ በመንቀሳቀስ ላይ ይገኛል።

በዮናይትድ ስቴትስ ውስጥ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ከሌሎች ህዝቦች በሚስተካከል መልኩ ወደ ቴክኖሎጂው ዘርፍ አለመቀላቀላቸው ሊያገኙት የሚችሉትን ጥቅም እንዳሳጣቸው የሚናገረው አዱኛ፣ የኮቪድ 19 ወረርሽኝ የፈጠረው የስራ ማፈናቀል እና የምጣኔ ሀብት ውጥንቅጥ ክስተት ብዙሃን ፊታቸውን ወደ መስኩ እንዲያዞሩ ማንቂያ ደወል እንደሚሆን ይጠቀማል።

ኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኙ የቴክኖሎጂው መስክ ባለሙያዎችም ክህሎታቸውን ለዓለም ገበያ ሊያቀርቡ የሚችሉበትን አማራጭም ይመክራል። ሀብታሙ ስዩም በመስኩ ዙሪያ የሚቀርቡ ጥያቄዎችን አሰናድቶ ከአዱኛ በቀለ ጋር አጭር ቆይታ አድርጓል።

መልካም ቆይታ !

ቴክኖሎጂ እና የመጻኢ ዘመን የስራ ገበያ ፦ቆይታ ከአዱኛ በቀለ ጋር
please wait

No media source currently available

0:00 0:08:49 0:00


XS
SM
MD
LG