በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

«የጠፈር ሳይንስ ቅንጡነት ሳይሆን ግዴታችን እየሆነ መጥቷል!» መ/ሐ/ዶ/ር ሮዳስ ታደሰ


መጋቢ ሃዲስ ዶ/ር ሮዳስ ታደሰ በጄቲቪ ያቀርቡት በነበረው «አንድሮሜዳ» የተሰኘ የፈለክ ጥናት(ዐውደ-ጠፈር) ትርኢት ይታወቃሉ።
መጋቢ ሃዲስ ዶ/ር ሮዳስ ታደሰ በጄቲቪ ያቀርቡት በነበረው «አንድሮሜዳ» የተሰኘ የፈለክ ጥናት(ዐውደ-ጠፈር) ትርኢት ይታወቃሉ።

የስነ-ፈለክ ፣ዐውደ-ጠፈር እና መሰል ሳይንሳዊ መስኮች ወዳጅ የሆኑ ኢትዮጵያዊያን መጋቢ ሐዲስ ዶ/ር ሮዳሰ ታደሰ እንግዳ አይሆኑባቸውም። ኢትዮጵያዊ ዕውቀትን የሚዘክሩ ከ20 በላይ ሃይማኖታዊ እና ሳይንስ ቀመስ መጽሃፍትን መጻፋቸው፣ የፈለክ -ጥናት የቴሌቭዥን መርሐ-ግብር ትርኢት ጀማሪ መሆናቸው ከሚጠቀሱላቸው ስኬቶች ጥቂቶቹ ናቸው።

ለአለፉት ሁለት ዓመታት ምንም ክፍያ ሳይጠይቁ ጄቲቪ በተሰኘ ቴሌቭዥን ጣቢያ ለተመልካች እንዳቀረቡት በሚናገሩለት «አንድሮሜዳ» የተሰኘ ትርኢት ላይ የላቀ አዕምሮ ባለቤት የሆኑ ህጻናት እና ታዳጊዎችን ለተመልካች አስተዋውቀዋል።ተመልካቾች ከቀጠናዊ ዕይታ ተሻግረው በምናብ የጠፈር ዓለምን ይዳስሱ፣ የስነ-ፈለክ ዕውቀታቸውን ያሳድጉ ዘንድ ለማስተማር ጥረዋል።

መርሐ-ግብሩ ይታይበት የነበረው የቴሌቭዥን ጣቢያ ለጊዜው ስራ ማቆሙን ተከትሎ የ« አንድሮሜዳ» ዕጣ ፋንታ አልታወቀም።« ኢትዮጵያዊ ሳይንስ እንደሌለ አዕምሯችን እንዲያምን በመደረጉ፣ዕውቀት ሁሉ ከውጭ ብቻ የሚገኝ እስኪመስለን ድረስ አድርሶናል» ሲሉ ቁጭታቸውን የሚሳሙት መጋቢ ሐዲስ ዶ/ር ሮዳስ ግን፣ የጀመሩትን ለማስፋፋት ያላቸውን ህልም ለአሜሪካ ድምጽ አጋርተዋል።

የአሜሪካ ድምጹ ሀብታሙ ስዩም ከመጋቢ ሐዲስ ዶ/ር ሮዳስ ታደሰ ጋር ያደረገውን ምጥን ቆይታ ያዳምጡ።

«የጠፈር ሳይንስ ቅንጡነት ሳይሆን ግዴታችን እየሆነ ይገኛል» መጋቢ ሀዲስ ዶ/ር ሮዳስ ታደሰ
please wait

No media source currently available

0:00 0:15:43 0:00


XS
SM
MD
LG