በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ጥቂት ስለ ሀገርኛው የመረዳጃ አውታር -«ደጋፊ»


ከዕወቅ ድጋፍ ማሰባሰቢያ አውታሮች መካከል አንዱ የሆነው ፋንድሊ በቅርቡ ይፋ እንዳደረገው በ2020 እኤአ በህዝባዊ መዋጮ(crowdfunding)አማካኝነት በመላ ዓለም ላይ ለተለያዩ ዓላማዎች የተሰበሰበው ገንዘብ ከ30 ቢሊየን ዶላር ይልቃል።ባለፈው የጎረጎሳዊያኑ ዓመት ብቻ ከስድስት ሚሊየን የሚበልጡ የህዝባዊ መዋጮ ዘመቻዎችን ዓለማችን አስተናግዳለች።

በመላ ዓለም ላይ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያንም በተለያዩ ጊዜያት በሚሊየኖች ዶላር የሚቆጠር ድጋፍ የተገኘባቸው ዘመቻዎችን አስተባብረዋል።ግለሰቦች እና ተቋማት ሊፈጽሟቸው ያሰቧቸውን ተግባራት ይፋ በማድረግ ፤መቀመጫቸውን በውጭ ሀገራት ባደረጉት GoFundMe እና KickStarter ን በመሰሉ አውታሮች በኩል፣አሊያም የቀጥታ ባንክ ሳጥኖችን በመክፈት ለጋሾች እንዲደግፏቸው በማድረግ የብዙሃንን ህይወት የታደገ ውጤቶችን አምጥተዋል።

መሰል ልምዶች አብነት ያደረገ ሀገርኛ የህዝባዊ መዋጮ አውታር ከሰሞኑ ስራ ጀምሯል።«ደጋፊ» የተሰኘው ፣ኢትዮጵያዊያን ለተለያዩ ዓላማዎች ገንዘብ ለማሰባሰብ ሲፈልጉ ቀደሚ ምርጫ ለመሆን የወጠነው አውታር ቢቲ በተሰኘ የቴክኖሎጂ ድርጅት የተሰራ ነው።

የድርጅቱ ኃላፊ አቶ ቢኒያም ነገሱ ማንኛውም የሚሰበሰብ ድጋፍ ለታለመለት ዓላማ ስለመዋሉ ጥብቅ የማረጋገጫ ርምጃዎችን እንደሚተገብር የተናገሩለትን አውታር በሚመለከት ከቪኦኤ ጋር ቆይታ አድርገዋል።

ሙሉ ጥንቅሩን ያዳምጡ፦

ስለ "ደጋፊ " አውታር፦ ምጥን ቆይታ ከቢኒያም ነገሱ ጋር
please wait

No media source currently available

0:00 0:07:39 0:00


XS
SM
MD
LG