በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኢትዮጵያ ሚዲያ ነፃነት አሁንም ከፈተና አልተላቀቀም


እ.ኤ .አ ጥቅምት 10/2016 ዓ. ም ኢንተርኔት ተዘግቶ በነበረበት ጊዜ ቡና እየጠጡ ጋዜጣ እያነበቡ። (ፎቶ ሙሉጌታ አየነ)
እ.ኤ .አ ጥቅምት 10/2016 ዓ. ም ኢንተርኔት ተዘግቶ በነበረበት ጊዜ ቡና እየጠጡ ጋዜጣ እያነበቡ። (ፎቶ ሙሉጌታ አየነ)

ለረጅም አመታት ለፕሬስ ነፃነት ከሚያሰጉ አገሮች ትመደብ የነበረችው ኢትዮጵያ ላለፉት ሁለት አመታት በመገናኛ ብዙሀን እንቅስቃሴ ዙሪያ በታዩ ለውጦች ምክንያት አለም አቀፍ አድናቆት ብታገኝም በኢትዮጵያ ያለው የፕሬስ ነፃነት አሁንም ከስጋት ነፃ አይደለም። የሚዲያ ፅንፈኝነት፣ የጋዜጠኞች የሙያ ብቃት እና በነፃነት ዙሪያ የታዩት መሻሻሎች ወደኃላ የመቀልበስ ስጋት አሁንም የሚዲያው ፈተናዎች ሆነው ቀጥለዋል።

የኢትዮጵያ ሚዲያ ነፃነት አሁንም ከፈተና አልተላቀቀም
please wait

No media source currently available

0:00 0:12:45 0:00

እነዚህ መሻሻያዎች የታዩበት የኢትዮጵያ ሚዲያ ግን ዛሬም ከፈተና አልወጣም። የሚዲያ ፅንፈኝነት፣ የሙያ ብቃት ማነስ፣ የመረጃ ማግኘት ችግርና የማህበረሰብ ሚዲያው በባህላዊው ሚዲያ ላይ እያሳደረ ያለው ተፅእኖ ዛሬም የሚዲያው ውስብስብ ችግሮች እንደሆኑ ቀጥለዋል።

ከዚህ ቀደም የአዲስ ነገር ጋዜጣ አዘጋጅ የነበረውና በስደት ስዊድን አገር የሚኖረው መስፍን ነጋሽ፣ የዋዜማ ሬዲዮ ዋና አዘጋጅ ነው። መስፍን በኢትዮጵያ ሚዲያ ዙሪያ የታዩት መሻሻሎች መረጃን በስፋት ከማዳረስ አንፃር ትልቅ ሚና እንዳላቸው ገልፆ፣ ነገር ግን ለረጅም ዘመን በጠላትነት ተፈርጀው የኖሩት የሚዲያ ተቇማት አሁን የሚፈለገውን ተቇማዊና ሙያዊ ሀይል ማቅረብ የሚችሉ አይደሉም ይላል።

መስፍን ጨምሮ የሙያ ብቃት ድንገት የሚገኝ ሳይሆን እየዳበረና እየተጠናከረ የሚሄድ ነው። የኢትዮጵያ ሚዲያ ደግሞ በብዙ መልኩ ሲኮረኮም የኖረ ከመሆኑ አንፃር ሙያው ውስጥ በመቆየት የሚዳብሩ ልምዶቸን እንዲያጣ ሆኗል ይላል።

በጋዜጠኝነት ሙያ ለረጅም ግዜ ያገለገለውና በሪፖርተር ጋዜጣ የፖለቲካ ጉዳዮች አዘጋጅ የሆነው ዩሀንስ አምበርብር፣ በሚዲያው ታየ የተባለውን ለውጥ በፍላጎት ደረጃ ከመግልፅ ያለፈ የመገናኛ ብዙሀን በሙሉ አቅማቸው እንዲንቀሳቀሱ የሚያስችል ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ አቅም ባለመፍጠሩ የሚዲያ ተቇማት ሙያዊ ብቃት ላይ መስራት አልቻሉም ይላል።

ሌላው ለኢትዮጵያ የሚዲያ ተቇማት ማደግ ትልቅ ተግዳሮት ሆኖ የሚገለፀውና፣ ጋዜጠኞች የሙያ ደረጃቸውን ከፍ እንዳያደርጉ የሚከለክላቸው ፅንፈኛና ሁላፊነት የጎደለው የሚዲያ እንቅስቃሴ ነው። የሚዲያ ተቇማት ወደ አንድ ርዕዮተ

አለም ማጋደላቸው ብቻውን ችግር አይደለም የሚለው መስፍን ዋናው ችግር ለህዝብ ትክክለኛና ሚዛናዊ መረጃ ማቅረብ አለመቻላቸው እና የአንድ አይነት አመለካከት ብቻ መጠቀሚያ መሆናቸው ነው ይላል።

ዩሀንስም ማህበረሰቡን የማሳወቅና የመቅረፅ ሀላፊነት የተጣለበት ሚዲያ ሀላፊነቱን ዘንግቶ የፅንፈኛ አመለካከቶች ማስፈፀሚያ ሆነዋል በሚለው ወቀሳ ይስማማል።

ህብረተሰቡን ለጉዳት የሚያጋልጡና ያልተጣሩ መረጃዎችን በማሰራጨት ረገድ ቀዳሚው ተወቃሽ ማህበረሰብ ሚዲያው ነው። ከዚህ አንፃር ይህ ወቀት ከየትኛውም ጊዜ በላይ የተጣራ መረጃ የሚፈለገበትጊዜ ነው የሚለው መስፍን፣ ባሀላዊ የሚዲያ ተቇማት የምንላቸው ጋዜጦች፣ ሬዲዮና ቴሌቭዝን ጣቢያዎች በማህበራዊ ሚዲያ ንፋስ ላለመወደድ መፍራትና መጠንቀቅ አለባቸው ይላል።

ሌላው ዩሀንስ ለሚዲያዎች ያልተቀረፈ ችግር ነው የሚለው መረጃ ፈልጎ ማግኝት ነው። በተለይ የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ቢሮ ከፈረሰ ወዲህ ከመንግስት መረጃ የሚገኝበት ወጥ አሰራር የለም የሚለው ዩሀንስ አያይዞም ከቅርብ ግዜ ወዲህ እየተስተዋሉ ያሉት የጋዜጠኞች እስርም በሚዲያ ተቇማት ላይ ፍርሀት እንዲያንዛብብ አድርጏል ይላል።

በእነዚህ ጉዳይ ያነጋገርናቸው የጠቅላይ ሚኒስትሩ የፕሬስ ሴክረታሪያት ሀላፊ የሆኑት አቶ ንጉሱ ጥላሁን በበኩላቸው ጫፍና ጫፍ ያሉ ሀሳቦች ገና ያልታረቁበት አገር ላይ የብሄርና የሀይማኖት ጥላቻዎች፣ እንዲሁም ግጭቶች እንዲካሄዱ የሚያደርጉ ቅስቀሳዎች በሚዲያዎች እንዳሉ ገልፀው መንግስት እነዚህን ተቇማት ማስተማር ይቀድማል ብሎ እየሰራ እንደሆነና እርምጃ መውሰድ ቀጣይ አካሄድ እንደሚሆን ያስረዳሉ።

በኢትዮጵያ ያለው የሚዲያ ነፃነት ሙሉ በሙሉ ገና የሚፈለገው ደረጃ ላይ አልደረሰም፣ በሽግግር ወቅትም እክሎች ያጋጥማሉ የሚሉት አቶ ንጉሱ መረጃ አሰጣጥን በተመለከተ ሁሉም የሚኒስቴር መስሪያቤቶችና ክልልሎች ራሳቸውን ችለው መረጃ እንዲሰጡ መደረጋቸውንና በጠቅላይ ሚኒስትሩ ዙሪያ የሚፈለጉ መረጃዎችን ደግሞ ፕሬስ ሴክሬታሪያቱ ይሰጣል ብለዋል። በኮሮና ቫይረስ ምክንያት የፕሬስ ነፃነት ቀን እንደቀድሞው በተለያዩ ዝግጅቶች ባይከበርም ቀኑ ግን በሚመለከታቸው ተቇማት ታስቦ እንደሚውልም አቶ ንጉሱ ነግረውናል።

ዘገባውን የማጠናቅቀው በዛሬው እለት የተከበረውን የፕሬስ ነፃነት ቀን አስምልክተው የአሜሪካ ድምፅ ሬዲዮ ዳይሬክተር አማንዳ ቤኔት ባስተላለፉት መልእክት ነው፡ አማንዳ ቤኔት በመልክታቸው በተለይ የተሳሳቱ መረጃዎች በበዙበት በዚህ ወቅት፣ ነፃ ሚዲያ ትክክለኛ መረጃዎችን ለመስጠት ወሳኝ ናቸው ብለዋል።

XS
SM
MD
LG