በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

«የሰራንበት ምክንያት አንድን ሃይማኖት ለመወከል ሳይሆን መልካም መልዕክትን ለማስተላለፍ ነው»


.
.

ከሰሞኑ መንፈሳዊ እና ዓለማዊ የኪነጥበብ ሰዎች የተጣመሩበት «የሰላም ሰው ነኝ» የተሰኘ ህብረ- ዝማሬ ለአድማጭ /ተመልካች ቀርቧል።ዘማሪያኑ ሶፊያ ሽባባው እና እስራኤል አቤል ከድምጻዊያኑ ዘሪቱ ከበደ፣ብሩክታዊት ጌታሁን እና ቻቺ ታደሰ ጋር በአቀንቃኝነት ተሳትፈውበታል።

ይህ ስራ በልዩ አቀራረቡ እና በሰነቀው መልዕክት ከብዙሃን መልካም ምላሽ የማግኘቱን ያህል ባልተለመደ መልኩ ዘማሪያን እና በተለምዶ ዓለማዊ ድምጻዊያን የሚባሉ ከያኒያንን ማቀናጀቱን በማንሳት የሚተቹትም አልጠፉም።

በስራው ላይ የተሳተፉት ድምጻዊ ብሩክታዊት ጌታሁን እና ገጣሚ ሰይፉ ወርቁ አድማጭ /ተመልካቾች ከምንም በላይ የህብረ-ዝማሬው መልዕክት ላይ ቢያተኩሩ እንደሚወዱ ለአሜሪካ ድምጽ ራዲዮ ተናግረዋል።

ቀጣዩ የጋቢና የኪነ-ጥበብ ቅኝት ሀሳባቸውን አካቷል።

«የሰራንበት ምክንያት አንድን ሃይማኖት ለመወከል ሳይሆን መልካም መልዕክትን ለማስተላለፍ ነው»
please wait

No media source currently available

0:00 0:08:49 0:00


XS
SM
MD
LG