በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ውርድወት ሃገር በቀል የምርምር ፕሮግራም


ውርድወት ሃገር በቀል የምርምር ፕሮግራም
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:49 0:00

የመብቶች እና የዴሞክራሲ እድገት ማሕበር(CARD) ውርድወት የምርምር ሥራ (ውርድወት ፌሌውሺፕ) በመጀመር  ለምርምር አድራጊዎች  የውድደር ጥሪ አቅርቧል፡፡ ይህ ምርምር ማኅበራዊ መበላለጦችን እንዲሁም በቁጥር አናሳ የሆኑ እና ለጥቃትና መድልዖ ተጋላጭ የሆኑ የማኅበረሰብ ክፍሎችን የእኩል ዕድል እና የእኩልነት መብት ተጠቃሚ ለማድረግ የሚያስችሉ አገር በቀል ዕውቀቶች እና ተሞክሮዎች ላይ እንዲሠሩ ድጋፍ የሚያደርግ መርሐ ግብር መሆኑ ታውቋል።

ውርድወት የምርምር ሥራ ፌሎውሺፕ መርሐ ግብር (ውርድወት ፌሌውሺፕ) ማኅበራዊ መበላለጦችን እንዲሁም በቁጥር አናሳ የሆኑ እና ለጥቃትና መድልዖ ተጋላጭ የሆኑ የማኅበረሰብ ክፍሎችን የእኩል ዕድል እና የእኩልነት መብት ተጠቃሚ ለማድረግ የሚያስችሉ አገር በቀል ዕውቀቶች እና ተሞክሮዎች ላይ ሴቶች እና ወጣቶች የምርምር ሥራ እንዲሠሩ ድጋፍ የሚያደርግ መርሐ ግብር እንደሆነ በ ካርድ ድረገጽ ላይ ተገልጿል።

ካርድ ውርድወት የምርምር ሥራ ፌሎውሺፕ መርሐ ግብር ሥያሜውን ያገኘው የቃቄ ውርድወት በተሰኝች እና በጉራጌ ዞን የዛሬ 160 ዓመታት በፊት በኖረች እና ለእኩል የጋብቻ መብት የታገለች ባለታሪክ ሴት ሰም መሆኑም ታውቋል።

የውርድወት ፌሎዎች ለሰባት ወራት የሙሉ ሰዓት ምርምር እንዲያደርጉ የሚጠበቅ ሲሆን፣ ካርድ የሥራ ቦታ በማዘጋጀት፣ ለምርመር የሚያገልገል በጀት በመመደብ እና በማማከር እንደሚያግዝም ታውቋል፡፡ ተወዳዳሪዎቹ ጥናታቸውን ሲጨርሱም ሁለት የምክክር መድረኮች እንዲያዘጋጁ የሚጠበቅ ሲሆን የምረመሩ ውጤትም ታተሞ ለባለድርሻ አካላት እንደሚሰጥም የካርድ ዳይሬክተር አቶ በፍቃዱ ሃይሉ ከአሜሪካ ድምጽ ጋረ በነበራቸው ቆይታ አስታውቀዋል፡፡የውርድወት ፌሎውሺፕ የማመልከቻ ቀን ገደብም ሚያዝያ 22፣ 2012 መሆኑ ታውቋል።

XS
SM
MD
LG