ዋሽንግተን ዲሲ —
ለወትሮው ከብት ለመግዛት የሚፈልግ ሰው፣ ወደ ልማዳዊ የከብት መሸጫ ስፍራዎች ማቅናት ፣እግር እስኪዝል ማማረጥ ፣ ጉሮሮ እስኪደርቅ የዋጋ ክርክር ማድረግ ይጠበቅበት ነበር። ኢትዮጵያዊያን ወጣቶች የጀመሩት አውታር ግን ይሄንን ልማድ ለማስቀረት ያለመ ይመስላል።
የራስ ገበያ የተሰኘው የበይነ መረብ ላይ የእንስሳት ግብይት አውታር፣ በመላው ሀገሪቱ የሚገኙ ሸማቾች እና ሻጮች ሁሉን ነገር "ኢንተርኔት" ላይ ጨርሰው እንስሳቱን እንዲረካከቡ የሚያደርግ መሆኑን መስራቾቹ ይናገራሉ።
ከሀብታሙ ስዩም ጋር አጭር ቆይታ ያደረገው የራስ ገበያ ተባባሪ መስራች እና ዋና ስራ አስኪያጅ መስፍን አበራ ስለ በይነ መረብ ላዩ የእንሳት ገበያ ያስረዳናል።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ