በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ከአነጋጋሪዎቹ የካርቱን ስዕሎች ባሻገር . . . ምጥን ቆይታ ከሰዓሊ ዓለማየሁ ተፈራ ጋር


ከዓለማየሁ ተፈራ ስላቃዊ ስዕሎች ጥቂቶቹ
ከዓለማየሁ ተፈራ ስላቃዊ ስዕሎች ጥቂቶቹ

መሐረብ አፏ ላይ ሸብ አድርጋ ከበላይዋ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ስራ አስኪያጅን ጭኖ የሚበር አውሮፕላንን በፍርሃት የምትመለከት ኢትዮጵያ ፣በተለያዩ ጥጎቿ ላይ ፈንጂዎች የተተከበሉባትን ሀገር ተሸክመው ከዘውግ ትብታብ እግራቸውን አላቀው ለመራመድ የሚታገሉ ጠቅላይ ሚኒስትር፣ጨቅላ ልጇን ሀሁ ለማስቆጠር የምትሞክር ፤ ልጇ ግን ቅንጡ ስልኩ ላይ ዐይኖቹን ተክሎ “እምቢ እንጃ !” የሚላት እናት።

እነዚህን እና መሰል የኢትዮጵያን እና የኢትዮጵያዊያንን ፖለቲካዊ፣ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ትርታዎች የሚከተሉ ስላቃዊ (የካርቱን )ስዕሎችን ማህበራዊ መገናኛዎችን የሚያዘወትሩ ያውቋቸዋል።የስዕሎቹ ፈጣሪ ዓለማየሁ ተፈራ ግን ሳቅ ከመፍጠር ወዲያ በስዕሎቹ መረር ያሉ እውነታዎች እና ማስገነዘቢያዎችን መመዝገብ የፈለገ ይመስላል።

ሀብታሙ ስዩም ከሰዓሊ ከዓለማየሁ ተፈራ ጋር ያደረገውን ምጥን ቆይታ ያድምጡ።

ከስላቃዊ ምስሎቹ ወዲያ... ቆይታ ከሰዓሊ አለማየሁ ተፈራ ጋር
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:01 0:00


የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG