No media source currently available
ዳዊት ጥበቡ ነዋሪነቱን በካናዳ ቶሮንቶ ያደረገ ኢትዮጵያዊ የፎቶ ባለሙያ ነው፡፡ በቶሮንቶ ጎዳናዎች ላይ በመዘዋወር የሚያገኛቸውን ከተለያዩ የዓለም ክፍል የመጡ መንገደኞችን እያናገረ ታሪካቸውን ከትቦ፤ ከፎቶግራፍ ጋር በማቀናጀት ‘ጉዞ ስቶሪስ’ በመባል የሚታውቀው የፎቶ ድር-ገፅ እና ኢንስታግራም ገፅ ላይ ያስቀምጣል፡፡ በዝዋይ ሃይቆች ላይም ከ200 በላይ ታሪካዊ ፎቶዎች ያሉበት “የጉዞ መፅሃፍም” አሳትሟል፡፡ ኤደን ገረመው እንዲ አሰናድታዋለች፡፡