No media source currently available
ከኢትዮጵያ በጉዲፈቻ በአሜሪካዊ ቤተሰቦች ተወስዳ ያደገችው ኢትዮጵያዊቷ ዲዛይነር አባይ ሹልዝ ወደ ትውልድ አገሯ ከዓመታት በፊት ተመልሳ፤ የገበያ ጥናት ማድረጕን ትናገራለች፡፡ ጥናቷን ስትጨርስም ዛፍ የተሰኝ የቆዳ ቦርሳ አምራች ድርጅት ከፍታ ከደርዘን በላይ ሴት ሰራተኞችን ቀጥራ እያሰራች ትገኛለች፡፡ የቪኦኤዎቹ ሃይዲ አዳምስ እና አቢ ሰን ስለ ስኬቷ አነጋግረዋታል፡፡ ኤደን ገረመው ወደ አማርኛ መልሳ እንዲ አዘጋጅታዋለች፡፡