በተማሪ ቤት የሚተዋውቁ ከአስር በላይ ወጣቶች ለአገራቸው ያላቸውን ለማበርከት እየተሰባሰቡ ምክር ጀመሩ፡፡ ለሚያዩዋቸው አብዛኞቹ የህብረተሰብ ችግሮች መነሻቸው የሴቶች አለመማር መሆኑን ተገነዘቡ፡፡ ስለዚህም ሴቶችን በቁዋሚነት ለመርዳት ምን እናድርግ የሚለውን ሃሳብ ማንሸራሸር ጀምሩ፡፡ ይህ ሂደት ግን ቀላል አልነበረም፡፡ ስለዚህም ብዙዎቹ ሳያስቡት በሕይወት ጉዳዮች እየተያዙ ቀሩ፡፡ ይሄን ሃሳብ ለመልቀቅ ያልፈቅዱ ሶስት ውጣት ሴቶች፡- ማስረሻ አየለ፣ ሳምራዊት መስነር እና ፍትህ አስራት ግን እ.ኤ.አ 2015 ዓ.ም ተምሳሌት ኪችንን መሰረቱ፡፡
ማንኛዋም ያለተማረች ሴት ልትስራው የምትችለው ነገር ቢኖር የምግብ ስራ መሆኑ ለተምሳሌት ኪችን መመስረት ምክንያት ሆኗል፡፡ በተምሳሌት ኪችን ውስጥ እራስን ማብቃት፣ መተጋገዝ፣ ትምህርት መማር፣ የሕክምና ውጪ ሽፋን፤ ገንዘብ መቆጥብ፣ አገልግሎት መስጠት፣ ተያይዞ ለማደግ መጣርን ሁሉም ተማሩበት፡፡ ተምሳሌት ከስራ ዕድል ውጪ ሁለንተናዊ ጥቅም የሚገኝበት በቅብብሎሽ ለሌሎች የሚተላለፍ ማሕበረስብ ተኮር የንግድ ስራ ድርጅት ነው፡፡
በአሁን ሰዓት ሁለተኛ ቅርንጫፉን በቦሌ ለመክፈት በዝግጅት ላይ የሆነው ተምሳሌት ሃያ ሶስት የሚሆኑ ሰራተኞች አሉት፡፡ ሙሉ ለሙሉ የሚያገኘውን ገቢ ሴቶችን ለማብቃት የሚጠቀምው ተምሳሌት፤ የንግድ ስራ ለመጀምር መነሻ ለሚፈልጉ ሴቶች የመነሻ ገንዘብ በብድር ይሰጣል፡፡ በአዲስ አበባ ቆሼ አካባቢ ላለ የምግብ ፕሮግራም እንጅራ፣ ፓስታ እና የተለያዩ ነገሮችን በዓይነት ይረዳል፡፡ ለዚህ ሁሉ መሳካት ታዲያ በተምሳሌት ኪችን አዘውታሪ የሆኑ በጎ ፍቃደኞች እና አጋር ወንዶችም አብረው እንዳሉበት ሰምተናል፡፡
ተምሳሌት ኪችንን መጠቀም እራሳቸውን እና ለሚፈልጉ ሴት ወጣኒያን ፕሮግራማቸውን እንዲያስተዋውቁ ቦታውን በነፃ ክፍት አድርጕል፡፡ ኤደን ገረመው የተምሳሌት ኪችን አጋር መስራች ፍትህ አስራት እና ከፕሮግራሙ ተሳታፊ እና ስራአስኪያጅ ፍሬህይወት ሽፈራሁ ጋር ቆይታ አድርጋለች፡፡