በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ከኢትዮጵያዊነት ወደ አፍሪካዊነት - የጥበብ ልጆች


ከኢትዮጵያዊነት ወደ አፍሪካዊነት - የጥበብ ልጆች
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:16 0:00

የኢትዮጵያ የትምህርት አሰጣጥ ሂደት ያለበትን እክል አይታ ከዛሬ 14 ዓመት በፊት የራሷን አስተዋፅኦ ለማበርከት ስራዋን የጀመረችው ብርከታዊት ጥጋቡ የጥበብ ልጆች ብላ የሰየመቻቸው ገፀባህሪያት በሌሎች የአፍሪካም አገራት ሊጓዙ በዝግጅት ላይ ናቸው፡፡

ብሩክታዊት ጥጋቡ ‘ፀሃይ መማር ትወዳለች’፤ ‘አሳተፉኝ’፤ ‘ትንሾቹ ጥያቂዎች’ እና ‘የጥበብ ልጆች’ የተሰኙ የሕፃናት የቴሌቪዥን ፕሮግራሞች አሏት፡፡ ስራዎቿ የንባብ እና የመጠየቅ ባህል እንዲዳብር እና ሴቶች ለጆችም እኩል ዕድል እንዲሰጣቸው ያስተምራሉ፡፡ የጥበብ ልጆች በተሰኙት የካርቱን ገፀ-ባህሪያት በመጠቀም ወጣት ሴት ልጆች ድፍረትን እንዲላበሱ፣ ያላቻ ጋብቻን፣ ግርዛትን እና በሴትነታቸው የሚደርሱባቸውን ጥቃቶች እንዲታገሉ ታበረታታለች፡፡ ኢትዮጵያ ወስጥ ባሉ 412 ት/ቤቶች ውስጥም ‘የፀሃይ ጥግ’ ኖሯት ተማሪ ልጆች ይወያዩባቸዋል፡፡

'ከ5 ሴት ህፃናት አንዷ ካለእድሜዋ ታገባለች' ሲባል ከተራ ቁጥርነት አልፎ ሊያሳሰበን፣ ሊያሰቆጨን ይገባል የምትለን ብሩክታዊት ጥጋቡ የኢትዮጵያ ሴት ሕፃናት ሕይወት ለማሻሻል ውይይት ለመፍጠር ብላ የፈጠረቻቸው ሶስቱ ልዕል-ሰብ ገፀ-ባህሪያት አገር አቋርጠው ድንበር ተሻግረው አህጉራዊ ለመሆን እየተንደረደሩ ነው፡፡

ኤደን ገረመው ከብሩክታዊት ጋረ የነበራትን ቆይታ እንዲ አሰናድታዋለች፡፡
XS
SM
MD
LG