ከ19 ዓመት በላይ በጥብብ ወስጥ ቆይታለች፡፡ ስራዎቿ በየቤታችን ቢደርሱም እስካሁን ድረስ ግን ብዙዎቻችን አናውቃትም፡፡ ከሃያ በላይ የቴሌቭዥን እና የሬዲዮ ድራማዎችን ፅፋለች፡፡ ‘ዝነኞቹ’ እና ‘ከሰላምታ ጋር’ የተሰኙ ሁለት የመድርክ ቲያትሮችን ለህዝብ አድርሳለች፡፡ በተለይ ከሰላምታ ጋር በተለያዩ አገራት ከአማረኛ ቕንቕ ወጪ በሰርቢያ፣ ጀርመንኛ መጀመሪያ በተፃፈበት እንግሊዘኛ 'Deseperate to fight' ተብሎ ተተርጉሞ በብሩንዲ፣ ኬንያ፣ ኡጋንዳ፣ ስዊድን እና ኒውዮርክ ታይቷል፡፡ በኒዎርክ ድራማ ት/ቤት ውስጥም የምስራቅ አፍሪካ ሴት ፀሃፍት ስራዎች ውስጥ ተካቶ ለማስተማሪያነት እያገለገለ ይገኛል፡፡
በአሁን ሰዓት በከፍተኛ ጉጉት የሚታየው ‘ደርሶ መልስ’ የቴሌቪዥን ድራማም ፀሃፊም ናት፡፡ የዛሬ የጥበብ ታዛ እንግዳች ጸሃፊ ተውኔት መዓዛ ወርቁ ናት፡፡ ከኤደን ገረመው ጋር ተከታዩን ቆይታ አድርጋለች፡፡
ትንሽ ድፍረት የፈጠራ ስራን እጅግ ያጎለብታል ትላለች- ፀሃፊ ተውኔት መዓዛ ወርቁ
የፕሮግራሙ ተከታታይ ክፍሎች
-
ማርች 03, 2021
ረቡዕ፡-ጋቢና VOA
-
ማርች 03, 2021
ኢትዮጵያ ውስጥ ወጣቶች የስራ ፈጠራ ሃሳባቸውን መሸጥ ይችሉ ይሆን?
-
ማርች 02, 2021
ማክሰኞ፡-ጋቢና VOA
-
ማርች 01, 2021
ፒስ ኮር - የሰላም ጓድ የበጎ ፈቃደኞች ድርጅት 60 አመት ሞላው
-
ማርች 01, 2021
ሰኞ፡-ጋቢና VOA