እንደ ኢትዮጵያ ላሉ እና ግብርና ከሰማኒያ በመቶ በላይ ምጣኔ ሃብታቸው ግብርና ለሆኑ አገራት ዘመናዊ ግብርና ቅድሚያ ሊሰጠው የሚገባ ነው፡፡ እምብዛም ሴቶች በማይደፍሩት በዚህ ሙያ ወስጥ ወጤታማ ሆና የአገሯን ገበሬዎች እየረዳች እና ሙያውን እያስተዋወቀች ትገኛለች፡፡
ኖላዊት ሺመልስ ትባላለች፡፡ የግብርና ባለሙያ ናት፡፡ የ2017 የማንዴላ ዋሺንግተን ፌሎሺፕ ፕሮግራም አሸናፊ በመሆን ወጣት አፍሪካዊ ተፅእኖ ፈጣሪ ወይም መሪ ወጣቶች መሃከል ሆናለች፡፡ የግብርና ሙያን ለወጣቶች ለማስተዋወቅ በማህበራዊ ድረ-ገፆች ላይ ትፅፋለች፡፡ በአሁን ሰአት በሩዋንዳ እና በኢትዮጵያ እየተንቀሳቅሰች ለግብርና ባለሙያዎች ስልጠና ትሰጣለች፡፡ ከኤደን ገረመው ጋር ቆይታለች፡፡