No media source currently available
በግጭት ምክንያት ከኦሮሚያና ከቤኒሻንጉል ክልል አዋሳኝ ወረዳዎች የተፈናቀሉ ሰዎች ወደየቀድሞ መኖሪያቸው መመለስ መጀመራቸውን የክልሎቹ የጋራ ሰላምና ልማት ማስተባበሪያ ፅህፈት ቤት አስታውቋል። የማቋቋሚያና በግጭቱ ወቅት የተፈጠረውን ቁስል የማከምና የማሻር ሥራ በቀጣይነት እንደሚከናወን የፅህፈት ቤቱ ኃላፊ አቶ ተሾመ ደሣለኝ ለቪኦኤ ተናግረዋል።