No media source currently available
ከተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች የተፈናቀሉ ቁጥራቸው ወደ አንድ ሚሊዩን የሚጠጉ ዜጎች ወደ የቀያቸው መመለሳቸውን የጠ/ሚ ጽ/ቤት አስታውቋል፡፡ መንግሥት ተፋናቃዮቹን መመለስ የጀመረው በቀድሞ የመኖሪያ አካባቢያቸው የነበረው የፀጥታ ሥጋት ለመወገዱ እርግጠኛ በመሆኑ ነው ሲሉ የጠ/ሚ ጽ/ቤት ቃል አቀባይ ቢል ለኔ ሥዩም ተናግረዋል፡፡