No media source currently available
የአፋር ፖሊስ አባላት 11 አርብቶ አደሮቸን ገደሉብኝ ሲል የሶማሌ ክልል መንግሥት ከስሷል፡፡ ግድውን ተከትሎ አፍደም አካባቢ የሚኖሩ ወጣቶች የኢትዮ ጂቡቲ ባቡር መስመርን የዘጉ ሲሆን ፌደራል ፖሊስ ሃዲዱን ለማስከፈት በወሰደው ዕርምጃ ሌላ ተጨማሪ አንድ ሰው ተገድሏል ተብሏል፡፡ የአፋር ክልል መንግሥት ግን ድርጊቱን መሰረተ ቢስ ውንጀላ ነው ብሎታል፡፡