No media source currently available
ራዕይ ለኢትዮጵያ ወይም ቪዥን ኢትዮጵያ የሚባለው የኢትዮጵያዊያንና ትውልደ-ኢትዮጵያ ምሁራን ስብስብ ኢትዮጵያ ውስጥ ሲያካሂድ የመጀመሪያ የሆነውን ስብሰባውን ባለፈው ወር አዲስ አበባ ላይ አካሂዷል። የጉባዔያቸው አካሄድ “አስደስቶናልም፤ ያስከፉንም ሁኔታዎች አሉ” ብለዋል ሊቀመንበሩ የሃርፐር ኢኮኖሚክስ ኮሌጅ ፕሮፌሰር የሆኑት ዶ/ር ጌታቸው በጋሻው።