No media source currently available
ከጋሞ ደሬዎች የአንዱ ካኦ ባሕላዊ መሪ ደምሴ ፃራ ይባላሉ፡፡ ቅዳሜ ዕለት በቡራዮ የተከሰተውን ግድያ በመቃወም በአርባ ምንጫ የተቃውሞ ሠልፍ ላይ፣ በቁጣ ንብረት ለማውደም የቃጡ ወጣቶች እንደነበሩ የሚታወስ ሲሆን፣ አንደ አካባቢው ባሕል ሣር ይዘው በአካላቸው ቆመው ንብረቱን ከጥፋይ ከተከላከሉ የጋሞ ሀገር ሽማግሌዎች አንዱ የማኅበረሠብ መሪም ናቸው ደምሴ ፃራ፡፡