No media source currently available
ጠ/ሚኒስትር አብይ አሕመድ እየወሰዷቸው ባሉ አውንታዊ እርምጃዎች በእጅጉ ተበረታተናል ሲሉ በኢትዮጵያ የዩናይትድ ስቴትስ አምባሳደር ማይክ ሬነር አስታወቁ፣ አሳሳቢ ለሆኑ ጉዳዮች ምላሽ ለመስጠት ኢትዮጵያ እያደረገች ያለችውን ጥረት ለመደገፍ፣ ሀገራቸው የምትችለውን ሁሉ እንደምታደርግም አምባሳደሩ አረጋግጠዋል፡፡