No media source currently available
በባሌ ዞን በሰዌና ወረዳ ቡርቃ ጠሬ በተባለ መንደር የሚኖሩ ነዋሪዎች ላይ የሶማሌ ክልል ልዩ ፖሊስ ተኩስ ከፍቶ ከአንድ ቤት ቤተሰብ አምስት ሰዎች ተገደሉ ሲሉ ለቤተሰቡ የቅርብ ምንጮችና አንድ የወረዳ አስተዳዳሪ ለአሜሪካ ድምፅ ተናገሩ። በተጨማሪም የልጆቹ እናትና አንድ ልጅ የመቁሰል አደጋ እንደደረሰባቸው ገልፀዋል።