No media source currently available
በደቡብ ኦሮሚያ በሞያሌ ከተማ ትናንት ማታ አንድ ሰው ባልታወቁ ሰዎች ተመቶ መሞቱና ሌላው ደግሞ በጥይት ተመቶ መቁሰሉ ተሰማ። ከሞያሌ ከተማ አራት ቀበሌዎች እጅግ በርካታ ነዋሪዎች መሰደዳቸው ታወቀ። እስካሁን ለማረጋጋት በተወሰደው እርምጃም በርካታ ሰዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን አንድ የኮማድ ፖስቱ ጽ/ቤት ተወካይ አስታወቁ።