በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የቢጫ ወባ መከላከያ ክትባት እና የዓለም ጤና ድርጅት ዘመቻ


ፋይል
ፋይል

“ከተሞች በፍጥነት እያደጉ ነው፤ እንቅስቃሴውም እንዲሁ። የአለማችን አየር ንብረት ለውጥ በወባ ትንኝ ምክንያት ለሚከሰቱ በሽታዎች መስፋፋት የራሱ የሆነ አስተዋፆ እያደረገም ይገኛል። ነገርግን ክትባቶችን በበቂ በማዳረስ ልንቆጣጠረው እንችላለን ብዬ አስባለሁ። ስለዚህ አላማችን በአለም ከመስፋፋቱ በፊት እንዴት ልንቆጣጠረው እንችላለን የሚለው ነው።” ታሪክ ጃሳርቪክ የዓለም ጤና ድርጅት ቃል አቀባይ።

በአንጎላና በኮንጎ ዲሞክራሲያዊት ሪፐብሊክ የቢጫ ወባ ወረርሽን ለመከላከል በተያዘ ጥረት ቁጥሩ ከ14 ሚልዮን የሚልቅ ሕዝብ የመከላከያ ክትባት ሊሰጠው መሆኑ ተዘገበ።

“በአፍሪቃ የመጀመሪያው ግዙፍ የመከላከያ ዘመቻ” ያለው የዓለም ጤና ድርጅት WHO ነው የአስቸኳይ ጊዜ የክትባት መርሃ ግብሩን የሚያስተባብረው።

እንዲህ ከፍተኛ ቁጥር የሚያሳትፍ የክትባት ዘመቻ ለወትሮው ከሦሥት እስከ ስድስት ወራት ዝግጅት ይጠይቃል።

ወረርሽኑ በስፋት ሊዛመት የሚችልበት የክረምት ወራት ከመግባቱ አስቀድሞ በመስከረም ወር መጀመር ጠይቃል።

ቢጫ ወባ በአብዛኛው በገጠራማ ቦታዎችና የመከላከያ ክትባትን በሚገባ በማይሰጥበት አካባቢዎች ላይ ነበር የሚታየው። የአለም አቀፉ የጤና ድርጅት WHO በከተማ ቦታዎች በከፍተኛ ሁኔታ በመታየትና ሰዎችን እስከሞት እያደረሰ ያለው የወባ ወለድ በሽታ በጣም እንዳሳሰበው ገልጿል።

እንደ የWHO ግምት ካለፈው የታሕሳስ ወር አንስቶ በቢጫ ወባ ወረርሽኝ ለህልፈት የተዳረጉትሠዎች ቁጥር በአንጎላ 369 በኮንጎ ዲሞክራሲያዊት ሪፐብሊክ 16 መድረሱንና በሁለቱ አገሮች ለወረርሽኙ የተጋለጡት ሠዎችም ቁጥር ከ6 ሺህ በላይ መገመቱን አመልክተዋል።

ዝርዝር ዘገባውን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያድምጡ።

የቢጫ ወባ መከላከያ ክትባት እና የዓለም ጤና ድርጅት ዘመቻ
please wait

No media source currently available

0:00 0:02:02 0:00

XS
SM
MD
LG