No media source currently available
የኢትዮጵያ የከፍተኛ ትምሕርት መግቢያ ፈተና መሰጠት ከማኅበራዊ መገናኛ ድረ ገጾች መዘጋት ጋር መያያዙ እያነጋገረ ነው። አቶ አበባው አያሌው በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሥነ ጥበብና ዲዛይን ት/ቤት የኢትዮጵያ ሥነ ጥበብና ታሪክ መምሕር ናቸው። በልዩ ልዩ ፖለቲካዊና ማኅበራዊ ጉዳዮች ትንታኔ በመስጠትም ይታወቃሉ። አቶ አበባው በዚህ ጉዳይ ላይ አስተያየት እንዲሰጡ ጽዮን ግርማ አነጋግራቸዋለች።