No media source currently available
ኢትዮጵያና ደቡብ ሱዳን ከጋምቤላ የተጠለፉትን ልጆች ለማስለቀቅ የሚያደርጉትን ጥረት በእጥፍ እንዲጨምሩ ሁለት የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብአዊ ጉዳይ ባለሞያዎች ጠይቀዋል። አጥፊዎቹ ለፍርድ መቅረብ እንዳለባቸውም አሳስበዋል። ባለፈው አርብ ሰባት ተጨማሪ ህፃናት መመለሳቸውን እና ወደ አገራቸው የገቡት ቁጥር 63 መድረሱን ደግሞ የጋምቤላ ክልል ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጋትሉአክ ቱት አስታውቀዋል።