No media source currently available
በአዲስ አበባ ከተማ ቦሌ ቡልቡላ ወረዳ 12 ቀበሌ ገበሬ ማኅበር፥ ልዩ ስሙ ወረገኑ በተሰኘ አካባቢ ሕገወጥ ናቸው የተባሉ ቤቶች እንዲፈርሡ መደረጋቸውን ነዋሪዎች ተናገሩ። ከፀጥታ ኃይሎች ጋር በተፈጠረ ግጭት በሰው ሕይወት ላይ ጉዳት መድረሱንም ያስረዳሉ። መንግሥት በጉዳዩ ላይ ምንም ዓይነት መግለጫ አልሰጠም።