ኢትዮጵያ ጥቃት ያደረስኩት እኔ ነኝ ሲል አርበኞች ግንቦት ሰባት ኃላፊነቱን ወስዷል
ሰሞኑን በደቡብ ኢትዮጵያ ጥቃት ያደረስኩት እኔ ነኝ ሲል አርበኞች ግንቦት ሰባት ኃላፊነቱን ወስዷል። የድርጅቱሊቀ መንበር ዶክተር ብርሃኑ ነጋ ዛሬ ከዝግጅት ክፍላችን ጋር ባደረጉት አጭር ቆይታ፥ ”ትግላችንን የምናካሂደው እዚያው ኢትዮጵያ ውስጥ ከኢትዮጵያ ሕዝብ ጋር ሆነን ነው” ብለዋል። የኤርትራ መንግሥት አሰልጥኖ የላካቸውን አሸባሪዎች በቁጥጥር ሥር ማዋሉን የብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎትናየፌዴራል ፖሊስ ፀረ-ሽብር የጋራ ግብረ ኃይል ማስታወቁ ይታወቃል።
የፕሮግራሙ ተከታታይ ክፍሎች
-
ጁን 01, 2023
በምዕራብ ትግራይ “ዘር ማጽዳት ተፈጽሟል” ሲል ሂዩማን ራይትስ ዋች አስታወቀ
-
ሜይ 18, 2023
የወለንጭቲ እና ቢሾፍቱ ከተሞች ጥቃት
-
ሜይ 15, 2023
የብሄራዊ እርቅ ጥያቄ ፈተናዎች
-
ኤፕሪል 27, 2023
የታንዛኒያው የሰላም ንግግር በቅድመ ድርድር ጉዳዮች ላይ እንደሚገኝ ተገለጸ