No media source currently available
ስፖርተኞች ህገ ወጥ ኃይል-ሰጪ መድኃኒቶችን እንዳይጠቀሙ የወጣውን ህግ ኬንያ አለማክበሯን፣ ዓለማቀፉ የፀረ-ኃይል-ሰጪ መድኃኒት መሥሪያ ቤት አስታወቀ። በዚህም ምክንያት ሪዮ ውስጥ በሚካሄደው የዘንድሮው የበጋ ኦሎምፒክስ ጨዋታዎች የመካፈል ዕድሏ አስጊ ደረጃ ላይ እንደሚገኝ ተገለጸ። የኬንያ ኦሎምፒክስ ኰሚቴ ግን፣ "ውሳኔውን ይግባኝ እላለሁ" ብሏል።