No media source currently available
ኬንያ ባለፈው ሳምንት ሁለት የስደተኞች መጠለያ ካምፖችን እንደምትዘጋ ስትገልጽ፣ ለዚህም ምክንያቷ የፀጥታ ስጋት እንደሆነ ማመልከቷ አይዘነጋም። አንዳንድ ተንታኞች፣ ከውሳኔው ጀርባ ሌላ ምክንያት መኖሩን ሲናገሩ ሌሎች ደግሞ፣ የጸጥታ ስጋት መኖሩን ይስማሙና፣ የስደተኞች መብት ግን ትኩረት ሊሰጠው እንደሚገባ ያሰምሩበታል።