No media source currently available
እሥላማዊ መንግሥት ነኝ የሚለው የሁከትና የሽብር ቡድን “ኢትዮጵያዊያንን ገድያለሁ” ስለማለቱ “ዝርዝር መረጃ ባይኖረንም “የኢትዮጵያዊያንን ልብ የሚሠብርና እጅግ የሚያሳዝን ድርጊት ነው” ሲሉ የኢትዮጵያ የመንግሥት ኮምዩኒኬሽንስ ጉዳዮች ፅሕፈት ቤት ኃላፊው አቶ ጌታቸው ረዳ ዛሬ በሰጡት መግለጫ ተናግረዋል።