በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኦፌኮ ከፍተኛ የአመራር አባላት በማረሚያ ቤት ከፍተኛ በደል ይደርስብናል አሉ


የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ (ኦፌኮ) ከፍተኛ የአመራር አባል አቶ በቀለ ገርባን ጨምሮ 22 በሽብር የተጠረጠሩ ተከሳሾች ዛሬ ለሁለተኛ ጊዜ በፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 19ኛ ወንጀል ችሎት ቀረቡ። እነ አቶ በቀለ በማረሚያ ቤት ስድብ ማስፈራራትና ሌሎችም ከፍተኛ ተጽኖዎች እንደተፈጸመባቸው ለፍርድ ቤቱ አቤቱታ አቅርበዋል። የማረሚያ ቤቱ ተወካይ አቤቱታውን አስተባብለዋል። ተከሳሾቹ በቀረበባቸው ክስ ላይ ያላቸውን አስተያየት እንዲሰጡ ለሌላ ጊዜ ተቀጥረዋል።

XS
SM
MD
LG