No media source currently available
በማሊ፣ በቡርኪና ፋሶና በአይቮሪኮስት ሆቴሎች ላይ የአሸባሪ ጥቃቶች ከተደጋገሙ ወዲህ ምዕራብ አፍሪቃ በተጠንቀቅ ሁኔታ ላይ ትገኛለች። አሁን ደግሞ ሾልከው የወጡ የጸጥታ ጉዳይ ሰነዶች እንዳመለከቱት ጋናና ቶጎ ከዐል-ቓዒዳ ጋር የተሳሰረው ጽንፈኛ ቡድን ቀጣዮቹ ኢላማዎች ናቸው። የጋና ፕረዚዳንት ጆን ማሀማ የሀገሪቱ እዝብ እንዲረጋጋ መክረዋል። የአሜሪካ ድምጽ ሬድዮ ዘጋቢ ፍራንሲስካ ካክራ ፎርሶን ከአንካራ የላከችውን ዘገባ አዳነች ፍሰሀየ ታደርሰናለች።